=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እንደሚታወቀው ጋብቻ አሏህ ለሰው ልጅ ከሰጠው ኒእማዎች መካከል አንዱ ነው። ትዳር የሰው ልጅ ከመጀመሪያው ሲፈጠር በትዳር የተረጋጋና ደስተኛ ሂወትን ይመራበት ዘንድ አሏህ ያስቀመጠው የስነ-ፍጥረት ህግጋት ሲሆን ኢስላም እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ ማህበረሰብ ባጠቃላይ የሰው ልጅ የትዳርን ጥቅም እንዲያገኙ ሁሌም ወደ ትዳር አለም ጥሪ ያደርጋል። ትዳር የሂወትታችን ወሳኝ ክፍል ሲሆን በኢስላም ልዩ ስፋራ ያለው የኢማናችን ግማሽ ነው።....Read more
ሴት ልጅ ከእናት አባቷ ቤት ከወጣችበት እለት አንስቶ በባል ቃልኪዳን ውስጥ ትገባለች። ከዚህም ጐንለጐን ባል ለሚስቱ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ኢስላም እንዲያሟላላት ሲያዘው፤ እሷን ደግሞ ለርሱ ታዛዥ እንድትሆን ያዛታል። ይህ ማለት ደግሞ ስብዕናዋን አጥታ ፣ መብቷን ተነጥቃ እንደባሪያ ዝቅ ትበል ማለት አይደለም። እራስን በባል ስር በማድረግ ታዛዥ መሆን ማለት እንጂ መጨቆን ወይም ሃሳብን በነፃነት አለመግለፅ ማለት አይደለም። ይልቁንስ ረዳት በመሆን ሃሳቧን ፣ አስተያየቷን እና ስሜቷን ለባሏ ማካፈል ማለት ነው።
እንዲያውም ብልህ ወንድ ማለት በራሱ ሃሳብ ብቻ ተደግፎ የመጨረሻ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት የሚስቱን ሃሳብና አስተያየት የሚጠይቅ ነው።....Read more
ክቡራን ወላጆች ልጆቻችን ከኻያሉ አሏህ የተሰጡን ጸጋዎች ናቸው። እነዚህን የዓይኖቻችነን ማረፊያዎች ፈጣሪያችን ሲሰጠን ግን ከተወሰኑ ሃላፊነቶችቶችና ግዴታዎች ጋር መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ይህ የኢስላም ሃይማኖት ሲሆን ቀና የሆነ ብቸኛ መንገድ ነው። እናም የአብራካችን ክፋዮች የሆኑ ልጆቻችነን በተገቢው መንገድ በማነፅ የነገውን ኢስላማዊ ትውልድ እንዲቀላቀሉና የአሏህ ባሮች እንዲሆኑ በትጋት መስራት ከእኛ ከወላጆች ይጠበቃል። ይህን ጉዳይ በማስመልከት ከሁሉም ነገር በላይ ተወዳጅ የሆኑት መልእክተኛ( ሰ.ዐ.ወ) ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል:-
ሁላችሁም እረኞች ናችሁ። ከምትጠብቁት ነገር ትጠየቃላችሁ። ባል የቤተሰቡ ጠባቂ ነው። ስለሆነም በቤተሰቡ ጉዳይ ይጠየቃል። ሚስት የባሏን ቤት ጠባቂ ናት። ስለሆነም የባሏን ቤት በተመለከተ ተጠያቂ ናት....Read more
እናት የዛሬ ማንነታችን ስትሆን በመልካም ስብዕና ኮትኩታ ፣ ከመጥፎ ነገር ከልክላ አሳድጋናለች። የወደፊት ግባችን ምን መሆን እንዳለበት ሁሌም ትጨነቃለች ፣ ታልማለች። እሷ ሳትበላ እኛን ታጐርሳለች፤ የራሷን ስሜት ገድባ የኛን ታሟላለች። ስናለቅስ ልቧ በፍርሃት ፣ በጭንቀትና በትካዜ ይዋጣል። እሩቅ ቦታ ስንሄድ ሃሳቧ ሁሉ ጥቅልል ብሎ ስለኛ ደህነነት ማሰብና መጨነቅ ይሆናል። በምን ሁኔታ ላይ እንደሆን ዘወትር ትጠበባለች።....Read more
የአብዱሏህ ቤተሰብ ጠንካራ ሙስሊሞች ሲሆኑ በዚህ ታሪክ ሐዲ የተባለ የዘጠኝ ዓመት ልጅ አላቸው። ሐዲ በትመህርት ቤት የሚሰጡ ፈተናዎችንና አሳይመንቶችን ይፈራና ይጠላ ነበር። ስፖርት መጫወት በክፍል ውስጥ ካለው ውድድርና ተሳትፎ ስኬት የበለጠ ቀላልና ምቹ እንደሆነ ያስባል። ቤተሰቦቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ይረዱት ዘንድ እንዲህ ሲል ይጠይቃል....Read more
ለምንሰራው ስራ ትኩረት እንስጥ
አብዛሃኛውን ጊዜ እኛ ወጣቶች ለምንሰራው ስራ ትኩረትን አንሰጥም። ረጋ ብሎ ከመስራት ይልቅ ነገራቶችን አቻኩለንና ነካ ነካ አድርገን ሰርተን እናልፋቸዋለን። ትምህርት ቤት ከገባን ጀምሮ የተወሰኑ መጽሐፎችን አንብበናል፤ ነገር ግን ንባባችን አትኩሮት የጐደለው ስለሆነ በእያንዳንዱ የክፍል ደረጃ በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን መውጣት አልቻልንም። ትእግስተኞችና ለስራቸው አትኩሮት የሚሰጡት ሲቀሩ።
ትንሽ አንብበን ብዙ መረዳትና ማብላላት ስንችል ብዙ ጊዜያችነን አቃጥለን ትንሽ እንረዳለን። ሰዎች መልዕክት አድርሱ ብለውን መልዕክቱ ይጠፋብናል ወይም ያልሆነ መልዕክት ተናግረን ችግር ይፈጠራል። ቤተሰቦቻችን ሱቅ ልከውን ያልሆነ ነገር ገዝተን እንመጣለን። ለዚህ ሁሉ ችግር ምክኒያቱ ለምንሰራው ስራ ትኩረት አለመስጠታቸን ነው። ለዚህም ዋናው መፍትሄ ሶላታችንን ስንሰግድ ምስጥ ብለን በሙሉ አትኩሮት መስገድ ነው። እናም ለሌሎች ለምንሰራቸው ስራዎች አትኩሮት ይኖረናል ማለት ነው።....Read more
እኛ የሰው ልጆች ማህበራዊ ፍጡሮች እንደመሆናችን ጓደኞች እንዲኖሩን እንፈልጋለን። አብዛሃኛዎቻኛው የሂወታችን ክፍል ከሰዎች ጋር በመቀላቀል ወይም ማህበራዊ ትስስር ከመፍጠር ጋር የተያያዘ ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደሚታወቀው ማህበራዊ ኑሮ በራሱ የጤናማ አኗኗር እና የችግር መፍትሄ ዋነኛ መሳሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሂወት ውጣ ውረድ የበዛበት የችግር ፣ የተስፋቢስነትና የውድቀት መንስኤም ነው።
ታዲያ ይህ ማህበረሰብ አባት ፣ እናት ፣ ልጅ ፣ እህት ፣ ወንድም ፣ አክስት ፣ አጐት ፣ ጓደኛ ፣ ጐረቤት እያለ የሚፈጠር ማህበራዊ ትስስር ሲሆን ይህ ትስስር ከጊዜ አንፃር እና እንደ የሰው ባህሪ እየተወሳሰበ ሂወት በፈተና የተሞላች ሆና መጥፎ ነገሮችን እንድንጋፈጥ እንሆናለን....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|